አባ አርቱሮ ሶሳ የቀድሞ ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮን ‘የእግዚአብሔር ሰው’ ብለው ጠርተዋቸዋል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
"ረጅም ዕድሜና ኃላፊነት ካለበት ሰው ከብዙ ገፅታዎች መካከል፣ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን 'የእግዚአብሔር ሰው' ልኬትን ማጉላት እፈልጋለሁ ብለዋል።
የኢየሱሳሳዊያን ማኅበር የበላይ አለቃ የሆኑት አባ አርቱሮ ሶሳ፣ በቫቲካን አቅራቢያ በሚገኘው የኢየሱሳዊያን ማኅበር የምኖሪያ ቤታቸው ሐሙስ ሚያዝያ 16/2017 ዓ.ም በሰጡት የጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የሟቹን የጳጳስ ሕይወት ማጠቃለያ አቅርቧል።
እርሳቸው የአርጀንቲና ተወላጅ የሆኑ የኢየሱሳዊያን ማሕበር አባል የነበሩ "አመስጋኝ ትውስታ" ገልጿል።
"ለሰዎች የነበራቸው አቀራረብ እና በኖሩበት በእያንዳንዱ አውድ ውስጥ ያለው ሁኔታ ከመንፈሳዊ ልምዱ እውቅና በመነሳት ብቻ ነው" ብለዋል።
ሟቹ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ይህን ዓለም ለሰው ልጆች ሁሉ ብቁ መኖሪያ እንዲሆን ለሰው ልጅ መለወጥ” የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ ሁል ጊዜ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በተግባር ለማዋል ይጥሩ ነበር ሲሉ አባ አርቱሮ ሶሳ ተናግረዋል።
አባ አርቱሮ ሶሳ አክለው እንዳሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የእርሳቸው አፈጻጸም በሌሎች ሰዎች መመዘኛዎች ለመለካት አይፈልጉም ነበር፣ ነገር ግን የኢየሱስን ወንጌል ለማዋሃድ እና ሁሉም ሰዎች ቅዱሳን እንዲሆኑ ለመጋበዝ ብቻ ነው የሰሩት ሲሉ አክለው ገልጸዋል። “ዋናው ነገር እርስ በርሳችን መደማመጥ ነበር” ሲል ተናግሯል።
ሟቹ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሁሉም ሰዎች የተከበረ ሕይወት እንዲኖሩ እና ዓለም በእውነት “ሁላችንም እንደ ወንድሞች እና እህቶች የምንኖርባት የጋራ ቤት” እንድትሆን ሕልም ነበራቸው ብለዋል።
አባ አርቱሮ ሶሳ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “በሰው ልጅ ውስብስብነት ላይ የእግዚአብሔርን መሐሪ እይታ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል የሚያውቁ እና ለጋራ ሕይወት ሰፊ ቦታዎችን ለመክፈት ሕይወታቸውን የሰጡ ሰው ነበሩ" ብሏል።
በማጠቃለያውም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን በመተካት ማንም ቢመረጥ ኢየሱሳውያን ስለ ተልእኮው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን ለመታዘዝ የገቡትን አራተኛ ቃል ኪዳን በታማኝነት እንደሚፈጽሙ አስታውሰዋል።