አባ ሮቤርቶ ፓሶሊኒ፥ “መሰናበትን መማር” በሚል ርዕሥ የመጨረሻውን የዐብይ ጾም አስተንትኖ አቀረቡ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
አባ ሮቤርቶ ፓሶሊኒ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2025 ዓ. ም ባደረጉት የዓብይ ጾም አራተኛ እና የመጨረሻ ስብከታቸው፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት ላይ በማስተንተን፥ የሚቻለው እና አስፈላጊው ሁሉ ሲፈጸም መሰናበትን ማወቅ እንዳለብን የሚገልጽ አስተንትኖአቸውን አቅርበዋል።
ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ባደረገው ስንብት፥ “ወደ ጎን በመሆን የታሪክን ነፃነት ወደ ነበረበት መመለስ እና የበለጠ ዓለም አቀፋዊ የሆነውን የተስፋ ወሰን ማስፋት እንደሚቻል አሳይቶናል” ሲሉ አስረድተዋል።
የኢየሱስ ክርስቶስ የመጨረሻ ግንኙነቶች
ከትንሣኤው በኋላ ኢየሱስ ክርስቶስ በብቸኝነት ምክንያት ፍርሃት እንዳይዛቸው ብሎ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር መገናኘቱን አስታውሰው፥ በተለይም መግደላዊት ማርያምን ሲሰናበታት የሞት ፍርሃትን እንድታሸንፍ መርዳቱን ተናግረዋል።
መቅደላዊት ማርያም በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ምክንያት ተስፋ ብትቆርጥም ጌታን ማወቅ የቻለችው ወደ ሕይወት ተስፋ እንደገና በጠራት ጊዜ እንደነበር ገልጸው፥ ይህ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ እኛን ሊመራን የሚፈልግ ትክክለኛ ለውጥ እና ይህም በሐዘን ተቆልፎ መቆየት የማይፈልግ፥ እራሱን በሌላ ሰው ልብ በኩል ለመግለጽ የሚፈቅድ የልብ መነቃቃት ነው” ሲሉ አስረድተዋል።
ዓለም ተገለበጠች
አባ ፓሶሊኒ በመቀጠልም፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመግደላዊት ማርያም የሰጣት ማስተዋል፥ ወደ ሰማይ ባረገ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ ሁሉ የተዳረሰ ማስተዋል እንደሆነም አስረድተዋል።
“አርባ ቀናቱ ምሳሌያዊ የፈተና ጊዜ ናቸው” ያሉት አባ ሮቤርቶ ፓሶሊኒ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በፍቅር መኖርን እንደመረጠ እና ይህም ከሙታን የተነሳውን እራሱን በሚያማልል እና በሚያስመስል ምስል በማሰር ፈተና ውስጥ እንደማይወድቁ በማረጋገጥ እንደ ሆነ አስረድተዋል።
የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የልዩ ልዩ ከፍተኛ የሐዋርያዊ ጽሕፈት ቤቶች ስብከት አቅራቢ አባ ሮቤርቶ ፓሶሊኒ እንደዚሁም፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ዓለም ትቶ በሄደበት ሁኔታ ተመልሶ እንደሚመጣ የገባው ቃል ኪዳን፥ በእግዚአብሔር ልጆች ህያው ምስክርነት አማካይነት እኛ በምንኖርበት ዓለም ውስጥ የሚሆን፣ በዘመኑ ፍጻሜ እንደሚሆን የሚጠበቅ የክብር መምጣት እንደሆነ አስረድተዋል።
የፍላጎት እና የሕይወት አንድነት
አባ ፓሶሊኒ በመጨረሻም፥ “የኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት እግዚአብሔር በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የተወው የሚመስለውን ማንኛውንም የኃይል ባዶነት ጸጸትን ያስወግዳል” ሲሉ አስረድተው፥ የኢየሱስ ክርስቶስ ወደ አብ መመለስ፣ “በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ከእርሱ ጋር አንድ መሆኑ፣ ለሌሎች ባበረከተው አገልግሎቱ እንዲገለጥ የታሰበ፥ ለፍጥረታት ሁሉ የሚዘረጋ፣ በምስክርነት እና በአገልግሎት መካከል የጠበቀ እና ጥልቅ ኅብረት እንዲኖር አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ እንደሆነ ገልጸዋል።
ያማረ እና አዲስ ነገር
በአስተንትኖአቸው ማጠቃለያም፥ የኢየሱስ ክርስቶስ አካል የሆኑት ክርስቲያኖች ቤተ ክርስቲያን እምነቷን እና ትውፊቷን በድጋሚ በምትገልጽበት በዚህ የኢዮቤልዩ ዓመት ውስጥ የወንጌልን እውነት በመያዝ እና በመመስከር፥ ዓለም በውስጣችን ያለውን የሚያምር እና አዲስ ነገርን መገነዘብ እንዲችል ለማድረግ እና እንዲሁም ታላቅ ዓለም አቀፍ የተስፋ ማዕበልን ማሳደግ እንደሚችሉ ገልጸዋል።
ክርስቲያኖች አዲስ ምስክሮች እና አስተባባሪዎች እንዲሆኑ የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው በተግባር ለመኖር አቅማቸውን ማስተባበር እንደሚችሉ ያላቸውን ተስፋ በመግለጽ ስብከታቸውን ደምድመዋል።