በሮም ታሪካዊ የኢዮቤልዩ በዓላቸውን ያከበሩ ታዳጊ ወጣቶች በሮም ታሪካዊ የኢዮቤልዩ በዓላቸውን ያከበሩ ታዳጊ ወጣቶች  

በሮም የተሰበሰቡት ታዳጊ ወጣቶች ታሪካዊ የኢዮቤልዩ በዓላቸውን አከበሩ

በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዕረፍት ምክንያት ቀኑ የተቀየረው የታዳጊ ወጣቶች ኢዮቤልዩ በዓል በሮም ከሚያዝያ 17-19 ተከብሯል። በበዓሉ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከዓለም ዙሪያ የመጡ በአሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ታዳጊዎች በሮም በተዘጋጀው በዓል ላይ ተሳትፈዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በሮማ ጎዳናዎች ላይ የታዩት ታዳጊዎች ክስተቱን “ታሪካዊ ነበር” ሲሉ ገልጸውታል። ከፈረንሣይ ሊዮን ሀገረ ስብከት ታዳጊ ወጣቶች ጋር የኢዮቤልዩ በዓልን ለማክበር ወደ ሮም የመጣችው የ14 ዓመት ዕድሜ ታዳጊ ቤያትሪስ ጉዞዋ የጣሊያናዊ ታዳጊ የብፁዕ ካርሎ አኩቲስ ቅድስና አዋጅ መስዋዕት ቅዳሴን ያካተተ እንደ ነበር ገልጻለች።

ታዳጊ ቤያትሪስ ከቫቲካን ዜና ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ፥ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን ዕረፍት ሲሰሙ የኢዮቤልዩ በዓላቸውን ያከብሩ እንደሆነ እርግጠኛ እንዳልነበረች ገልጻ፥ እንደ ዕድል ሆኖ እግረ መንገዱን በዓሉንም ማክበሯን ተናግራለች።

ታዳጊዎች በሮም ታሪካዊ የኢዮቤልዩ በዓላቸውን ሲያከብሩ
ታዳጊዎች በሮም ታሪካዊ የኢዮቤልዩ በዓላቸውን ሲያከብሩ

በሟቹ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይ ለመገኘት በመቻሉ አመስጋኝነቱን የገለጸው በፈረንሳይ የሊዮን ሀገረ ስብከት ታዳጊ አርቱር በበኩሉ፥ “ርዕሠ ሊቃነ ጳጳት ፍራንችስኮስ ተልዕኮዋቸውን ፈጽመዋል” ሲል ገልጿል።

ወደ ቅዱስ ፍራንችስኮስ አገር አሲሲ መሄዳቸውን የተናገረችው ጓደኛቸው ዞዬም፥ “ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን ያነሳሳቸው ምን እንደ ሆነ አሁን ተረድተናል” ስትል አክላለች። ቅዱስነታቸውን የሚያውቋቸው ለታዳጊዎች ትኩረት እንደሚሰጡ እንደ ነበር ገልጸው አድናቆታቸውን ገልውላቸዋል።

ቅዳሜ ሚያዝያ 18/2017 ዓ. ም. በተፈጸመው የቅዱስነታቸው የቅዱስነታቸው የቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኘችው ስዊዘርላንዳዊ ሐና በበኩሏ፥ የወጣቶች ኢዮቤልዩ በዓል የሐዘን እና የምስጋና ጊዜ እንደ ነበር፥ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወጣቶችን ይቀርቡ እንደ ነበር ገልጻ፥ ፈገግታቸው የሁሉንም ሰው ልብ በሚነካ መንገድ እንደ ነበር አስታውሳለች።

ቤያትሪስ ለሟቹ የሮም አቡን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ክብር ከሰጡት ምዕመናን መካከል መገኘቷን እንደምታደንቅ ተናግራለች።

ወጣቶች ይህን ልዩ ልምድ እንዲጋሩ ላደረጉት የቡድን መሪዎች ማስተካከያዎችን ማድረግ እንደ ነበረባቸው፣ ከሟቹ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ለመገናኘት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ሁሉም የመጨረሻውን ስንብት ለማድረግ በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ መገኘት መቻላቸው ታውቋል።

ሌላው የታዳጊ ወጣቶች ኢዮቤልዩ ድምቀት የሆነው የብፁዕ ካርሎ አኩቲስ የቅድስና አዋጅ ለሌላ ቀን የተላለፈ ቢሆንም እሑድ ዕለት በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ በደስታ የተሞሉ ታዳጊ ወጣቶች ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ክብር ሲባል በተዘጋጀው ዘጠኝ የሐዘን ቀናት መካከል በሁለተኛ ቀን የመስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተሳትፈዋል።

 

28 Apr 2025, 17:33