ቻይናዊ ሰዓሊ ያን ፒ ሚንግ “ከግድግዳ ባሻፈር” የተሰኘ የሥነ-ጥበባዊ ሥራ ቻይናዊ ሰዓሊ ያን ፒ ሚንግ “ከግድግዳ ባሻፈር” የተሰኘ የሥነ-ጥበባዊ ሥራ 

ቫቲካን በማረሚያ ተቋማት ውስጥ ባለው የባህል ሚና ላይ ያተኮረ ስብሰባ እንደሚያዘጋጅ ተገለጸ

በቅድስት መንበር የባሕል እና የትምህርት ጉዳዮች ምክር ቤት ከመገናኛ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር፥ ባህል በማረሚያ ተቋማት ውስጥ ሊጫወት በሚችለው ሚና ላይ ያተኮረ ስብሰባ ማዘጋጀታቸው ተገለጸ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ሐሙስ ሚያዝያ 2/2017 ዓ. ም. በቫቲካን ውስጥ በሚገኝ በቅዱስ ፒዮ አሥረኛ አዳራሽ ውስጥ በሚካሄድ ላይ ከአካዳሚው ዓለም የተወጣጡ የኪነ ጥበብ ሰዎች፣ ጋዜጠኞች እና ከባህል ዙሪያ የተውጣጡ ሰዎች እንደሚካፈሉት ታውቋል።

“ባህል በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ሕይወት ነው” በሚል ርዕስ ሐሙስ መጋቢት 2/2017 ዓ. ም. በቅዱስ ፒዮ አሥረኛ አዳራሽ ውስጥ የሚካሄደውን ስብሰባ በጋራ ያዘጋጁት፥ በቅድስት መንበር የባሕል እና የትምህርት ጉዳዮች ምክር ቤት ከመገናኛ ጽሕፈት ቤት ጋር በመሆን እንደሆነ ታውቋል።

ስብሰባውን የሚመሩት፥ ጣሊያናዊው ጋዜጠኛ ሪካርዶ ኢኮና ከአካዳሚው ዓለም ከተወጣጡ የኪነ ጥበብ ሰዎች፣ ጋዜጠኞች እና የባህል ጠበብት ጋር በኅብረት ሲሆን፥ ባሕል በማረሚያ ቤት ውስጥ ያለውን እሴት ለማሳደግ፣ ለማጎልበት እና ሰብዓዊ ክብርን ለማስጠበቅ እንደሆነ ታውቋል።

ብዙ የዕውቀት ዘርፎችን የሚወክል ስብሰባ

ስብሰባውን በኅብረት የሚከፍቱት በቅድስት መንበር የባሕል እና የትምህርት ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚደንት ብጹዕ ካርዲናል ቶሌንቲኖ ዴ ማንዶካ፥ በቅድስት መንበር የመገናኛ ጽሕፈት ቤት ተጠሪ ዶ/ር ፓውሎ ሩፊኒ እንደሚሆኑ ታውቋል።

በስብሰባው ላይ ጥናታዊ ጽሑፎቻቸውን የሚያቀርቡት ከሮም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ የተጋበዙ ስቴፋኖ አናስታሲያ፣ የኪነ ጥበብ ባለሞያ ላውሪ አንደርሰን፣ የቫቲካን ሬዲዮ ጋዜጠኛ ሮቤርታ ባርቢ፣ ደራሲ እና አዘጋጅ ሮዛ ጋላንቲኖ፣ የሬዲዮ ጋዜጠኛ ቴሬዛ ፓውሊ፣ ከሮም ላ ሳፒየንዛ ዩኒቨርሲቲ ፒሳና ፖሶኮ እና ማርታ ማርኬቲ፣ የፓስቲፊቾ ሴሬሬ ፋውንዴሽን የጥበባ ዳይሬክተር ማርቼሎ ስማሬሊ እና አርቲስት ቶማሶ ስፓዚኒ ቪላ እንደሆኑ ታውቋል።

የፕሮጀክቶች አቀራረብ

በዝግጅቱ ላይ በርካታ የትናንት፣ የዛሬ እና የወደፊት ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ በማረሚያ ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ሥራዎችን የተመለከቱ ፕሮጀክቶች ይቀርባሉ። ታዋቂው አርቲስት እና አቀናባሪ ላውሪ አንደርሰን እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1998 ዓ. ም. በሳን ቪቶር ማረሚያ ቤት ለፕራዳ ፋውንዴሽን የተሰራ “ዳል ቪቮ” የተሰኘ እና እንዲሁም ከ2015 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየ “ሃቤያስ ኮርፑስ” ፕሮጀክት እና ከጓንታናሞ ቤይ የመጣውን ወጣት እስረኛ የሚያሳይ ፊልም እንደሚቀርብ ታውቋል።

በቅድስት መንበር የባሕል እና የትምህርት ጉዳዮች ምክር ቤት የዘመናዊ ሥነ-ጥበብ ክፍል ሃላፊ ክሪስቲና ፔሬላ የጥበባዊ ሥራዎችን የምታቀርብ ሲሆን፣ ቻይናዊ ሰዓሊ ያን ፒ ሚንግ “ከግድግዳ ባሻፈር” የተሰኘ ሥነ-ጥበባዊ ሥራውን እንደሚያቀርብ ታውቋል። የጥበብ ሥራዎች በተጨማሪ ከቫቲካን በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ እና ሬጂና ቼሊ በመባል በሚታወቅ ማረሚያ ቤት የሚኖሩ እና የሚሠሩ ሰዎችን የሚያሳዩ 27 የቁም ምስሎችን ያቀፈ እንደሚሆን ታውቋል።

ዝግጅቱ በቫቲካን ዩቲዩብ በጣሊያንኛ ቋንቋ በቀጥታ ስርጭት እንደሚቀርብ ታውቋል።

 

09 Apr 2025, 15:24