ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ ስለቀብራቸው ሁኔታ ቀደም ሲል ያደረጉት ኑዛዜ
የምድር ህይወቴ መጨረሻ እየተቃረበ እንደሆነ እና በዘላለም ህይወት ላይ ህያው ተስፋ እንዳለኝ እየተሰማኝ፣ የእኔን የመካነ መቃብር ቦታ በተመለከተ ብቻ ፈቃዴን መግለጽ እፈልጋለሁ።
የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ሕይወቴን እና ክህነታዊኑ የርዕሰ ሊቃነ ጵጵሳና አገልግሎቴን ለጌታችን እናት ለቅድስት ድንግል ማርያም ሁልጊዜ አደራ ሰጥቻለሁ። ስለዚህ የትንሣኤን ቀን በመጠባበቅ ላይ እንዳለ ሟች ዕረፍቴን በሳንታ ማሪያ ማጆሬ ባዚሊካ ውስጥ እንዲፈጸም እጠይቃለሁ።
በእያንዳንዱ ሐዋርያዊ ጉዞ መጀመሪያ እና መጨረሻ ላይ ለጸሎት በሄድኩበት በዚህች ጥንታዊት የማርያም ቤተ መቅደስ የመጨረሻ ምድራዊ ጉዞዬ እንዲያበቃ እመኛለሁ፣ ሐሳቤን ንፁህት በሆነች እናት ጥበቃ አደራ በመስጠት፣ ስለ አስተዋይ እና የእናትነት እንክብካቤዋ አመሰግናለሁ።
መካነ መቃብሬ በጳውሎስ የጸሎት ቤት (በሳናታ ማሪያ ማጆሬ ባዚሊካ ውስጥ በሚገኘው የሳሉስ ፖፑሊ ሮማኒ 'የሮም ሕዝብ ጠብቂ' የጸሎት ቤት) ውስጥ እንዲከናወን እና ከላይ በተጠቀሰው የጳጳስ ባሲሊካ ስፎርሳ የጸሎት ቤት መካከል ባለው የጎን ዝግ ክፍል ውስጥ እንዲዘጋጅ እጠይቃለሁ ።
መቃብሩ በምድር ውስጥ መሆን አለበት፣ ቀላል ፣ ለየት ያለ ጌጥ የሌለው እና ብቸኛው የመቃብር ራስጌ ጽሑፍ-'ፍራንችስኮስ' የሚለው እንዲሆን ጠይቃለው።
ለመቃብሬ ዝግጅት ወጪዎች የሚሸፈኑት እኔ ባዘጋጀሁት የበጎ አድራጎት ገንዝብ ነው፣ ገንዘቡ ወደ ሳንታ ማሪያ ማጆሬ የጳጳስ ባዚሊካ እንዲዛወር እና ለዚህም ለየኔታ አባ ሮላንዳስ ማኪርካስ መመሪያ ሰጥቻለሁ።
ለእኔ መልካም ለተመኙ ሰዎች ሁሉ ጌታ የሚገባውን ሽልማት ይስጥ፥ ስለ እኔ መጸለይ ቀጥሉ። በመጨረሻው የሕይወቴ ክፍል ላይ ያለውን መከራ ለአለም ሰላም እና በሕዝቦች መካከል ወንድማማችነትን ይሰፍን ዘን ለጌታ በአደራ አቀርባለሁ።
እ.አ.አ ሰኔ 29/2022 ዓ.ም