ፈልግ

ካርዲናሎች የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን መቃብር ጎብኝተው ጸሎት ማድረጋቸው ተገለጸ!

የብፁዕ ካርዲናሎች ኮሌጅ (ሕብረት) አባላት የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን በቅድስት ማርያም ሜጀር የጳጳስ ባዚሊካ የሚገኘውን መቃብራቸውን ጎበኙ፣ በመቀጠልም የምሽት ጸሎት ማድረጋቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በዕለተ ትንሳኤ ሁለተኛ እሑድ መለኮታዊ ምሕረት እለት ሰንበት መገባደጃ ላይ የብፁዕን ካርዲናሎች ኮሌጅ (ሕብረት) አባላት ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ ለሕዝብ በተከፈተው መቃብራቸው የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን  ክብር ለመስጠት እና ለመጸለይ ወደ ማርያም ሜጀር ቤተ ክርስቲያን ማቅናታቸው ተገልጿል።

ከዚያም በባሲሊካ አስተባባሪ ሊቀ ካህናት፣ የሊቱዌኒያ ካርዲናል ሮላንዳ ማኪሪካስ መሪነት የማታ ጸሎት ማድረጋቸው ተገልጿል።

በወቅቱ ይህንን የማታ ጸሎት ምዕመናንም የተቀላቀሉ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በጸሎት ሥነ-ሥረዓቱ ላይ ለቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ያላቸውን አክብሮት ለመግለጽ በሥፍራው መገኘታቸው ተዘግቧል። ከጠዋት ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ ሃያ ሺህ የሚገመቱ ሰዎች መቃብሩን ጎብኝተው ነበር።

28 Apr 2025, 11:16