የቫቲካን የቁጥጥር እና የፋይናንስ ባለስልጣን መሻሻል የታየበትን የገንዘብ ሪፖርት አቀረበ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
የቁጥጥር እና የፋይናንስ መረጃ ባለስልጣኑ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2024 ዓ. ም. ባወጣው ሪፖርቱ፥ የቅድስት መንበር እና የቫቲካን መንግሥት ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን፣ ሽብርተኝነትን እና የጅምላ ጨራሽ የጦር መሣሪያ ስርጭትን ለመከላከል ሚያደርጉትን ጥረት ማጠናከር መቀጠላቸውን አስታውቋል።
አጠራጣሪ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን ሪፖርት ማድረግ
የቁጥጥር እና የፋይናንስ መረጃ ባለስልጣኑ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ 2024 ዓ. ም. ባወጣው ሪፖርቱ፥ የ79 አጠራጣሪ የገንዘብ እንቅስቃሴ ሪፖርቶችን መቀበሉን ገልጾ፥ በ 2023 ከተቀበለው 123 ጋር ሲነፃፀር ቀንሶ መገኘቱን እና ይህም ከሪፖርት አቅራቢዎቹ ድክመት ይልቅ የጥራት መጨመርን የሚመለከት በመሆኑ እንደ አወንታዊ ውጤት መቆጠሩን አስታውቋል።
የቁጥጥር እና የፋይናንስ መረጃ ባለስልጣኑ በሪፖርቱ ላይ እንዳብራራው፥ አዝማሚያው በዋነኝነት የሚገለጠው የሪፖርቶቹ ምርጫ ሂደት ደረጃ በደረጃ መሻሻል እና እንደ ውስጣዊ እና ዓለም አቀፍ ትብብር መጨመር ባሉ አመላካቾች እንደሚታይ አስረድቷል።
“አጠራጣሪ ተግባራትን በሪፖርት ማቅረቡ ዋና የሆነው የገንዘብ ሥርዓት መጠናከር ተጨማሪ ማረጋገጫ እና ክትትል በሚደረግበት አካል ላይ ዒላማ ያደረገ ፍተሻ ውጤት ነው” ሲል አስረድቷል። ባለስልጣኑ አክሎም በቂ ቁርጠኝነት፣ አጠቃላይ ውጤታማ ድርጅታዊ የሥርዓት ሂደትን ለማሻሻል የተመረጡ ቦታዎችን ለማስተካከል ዕቅድ መዘጋጀቱን አስታውቋል።
ቀጣይነት ያለውን ክትትል እና ቁጥጥር ለማድረግ የስልጠና እንቅስቃሴዎችን እንደገና መጀመር የቁጥጥር እና የፋይናንስ መረጃ ባለስልጣኑ ቀጣይነት ያለውን ቁርጠኝነት የሚደግፍ ጠቃሚ ተግባር እንደሆነ ተገልጿል።
ለመልክአ ምድራዊ አደጋዎች የበለጠ ትኩረት መስጠት
የባለስልጣኑ የ2024 ዓመታዊ ሪፖርት፥ አጠራጣሪ የገንዘብ እንቅስቃሴን በሚያሳዩ ሪፖርቶች መካከል ያለውን ልዩነት ገልጾ፥ በተጠቀሰው ዓመት ውስጥ ያልተለመዱ ምልክቶች እና አመለካከቶች ለመጀመሪያ ጊዜ መቅረባቸውን እና እነዚያ ሪፖርቶች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሊያጋጥሙ ከሚችሉ ከፍተኛ አደጋ ጋር ወይም የተሻሻለ ክትትል ከሚደረግባቸው አካባቢዎች ጋር የተያያዙ እንደሆነ አስረድቷል።
የታየው ለውጥ ከፍተኛ አዳዲስ ዘዴዎች ሥራ ላይ መዋላቸውን ያመላክታል ያለው ሪፖርቱ፥ ይህም “ጂኦግራፊያዊ አደጋ” ለሚባለው ልዩ ትኩረትን ያሳየ፥ የቁጥጥር እና የፋይናንስ መረጃ ባለስልጣን በዓለም ዙሪያ በተለይም የቤተ ክርስቲያን መገኘት እጅግ አስፈላጊ በሆኑ ክልሎች ውጤታማ እና ወሳኝ የሆነ ሙያዊ የገንዘብ እንቅስቃሴዎችን የሚያከናውን ብቸኛው የቤተ ክርስቲያን አካል እንደ ሆነ ታውቋል። ሆኖም ግን ባለስልጣኑ ከእነዚህ ሪፖርቶች ውስጥ አንዳቸውንም ለፍትህ ቢሮ ሪፖርት እንዲላክ አለማድረጉ ታውቋል።
የቅድስት መንበር የሃይማኖታዊ ሥራዎች የገንዘብ ተቋም ጠንካራ እና በሚገባ የተደራጀ አካል ሆኖ እንደሚቆይ ተገልጿል። ተቋሙ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2024 በፈጸመው ሥራው አስተዋይነት እና ዘላቂነት ባለው አስተዳደሩ ከሃይማኖት ሥራዎች ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ገጽታዎች ሳያቋርጥ ስልታዊ ግምገማዎችን በማድረግ አከናውኗል።
በቅርብ ቁጥጥሩ የአስተሳሰብ ደንቦችን እና የአሰራር ገደቦችን በማክበር በክልሉ ሙያዊ የፋይናንስ እንቅስቃሴን እንዲያካሂድ የተፈቀደለት ብቸኛው ተቋም ሲሆን፥ የፋይናንስ እንቅስቃሴን ከመከታተል ጋር “የክትትል ግምገማ ሂደት የሚቆጣጠር” (SREP) እየተባለ የሚጠራውን ተቋም በማጥራት ስለ አካባቢያዊ እና ማህበራዊ ስጋት መረጃ የሚያወጣበትን መስፈርቶች በማስተዋወቅ ለፋይናንስ ዘርፉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል። ዶ / ር ካርሜሎ ባርባጋሎ የእነዚህ ሁሉ ተግባራት ውጤቶች በዓመታዊ ሪፖርቱ በኩል ሲያስተዋውቁ እንደገለጹት፥ በቅድስት መንበር የሃይማኖታዊ ሥራዎች የገንዘብ ተቋም በኩል የተገኙ መልካም ውጤቶች ተቋሙ እንደ ጠንካራ እና በሚገባ የተደራጀ አካል እንደሆነ ገልጸዋል።
የአውሮፓ የገንዘብ ተቋም ማሻሻያዎች መኖራቸውን አረጋግጧል
የ2024 ዓመታዊ ሪፖርት በተጨማሪም የአውሮፓ የገንዘብ ኮሚቴ በቴክኒካዊ ተገዢነት ላይ በተደረገው ክትትል አወንታዊ ውጤት፥ ማለትም የስልጣን ተቆጣጣሪ ማዕቀፍ ከፋይናንስ እርምጃ ግብረ ሃይል (FATF) መመዘኛዎች ጋር ምን ያህል እንደሚጣጣም አሳይቷል።
5ኛው ዙር የጋራ ግምገማ እንደሚያመለክተው፥ ቅድስት መንበር፥ የቫቲካን ከተማ ግዛትን ጨምሮ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በሚያዝያ ወር 2021 ዓ. ም. የተደረገው የእርስ በርስ ግምገማ ሪፖርትን ተከትሎ የተደረጉ ለውጦችን ገምግሟል።
የፕሬዚዳንቱ ደብዳቤ
ዶ/ር ባርባጋሎ በሪፖርቱ መግቢያው ላይ እንደገለጹት፥ የቁጥጥር እና የፋይናንስ መረጃ ባለስልጣን እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ 2024 ባወጣው ሪፖርት፥ በቅድስት መንበር የሃይማኖታዊ ሥራዎች የገንዘብ ተቋም የገንዘብ ማጭበርበርን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወሰደው እርምጃ ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እንቅስቃሴ ለመግታት ከፍተኛ ክትትል መደረጉን አረጋግጠዋል።
ይህ ከሀገር ውስጥ እና ከዓለም አቀፍ ባለስልጣናት ጋር ያለው የትብብር ጥራት እንዲሁም በቅድስት መንበር የሃይማኖታዊ ሥራዎች የገንዘብ ተቋም በኩል የተገኙ መልካም ውጤቶችን የሚመሰክር መሆኑን ገልጸዋል።
ዶ/ር ባርባጋሎ አክለውም፥ “ባለሥልጣኑ ከሚያከናውኗቸው ተግባራት መካከል የሁለቱን አግባብነት ሲያጎሉ፥ በአንድ በኩል ቀጣይ የማገገሚያ ሂደትን በሚገባ ለማከናወን የሚያስችል የመለየት አቅም ማሳደግ መቻሉ፥ በሌላ በኩል በሕገ-ወጥ መንገድ የሚገኝ የገንዘብ ማጭበርበር መከላከል እንዲችሉ ለቫቲካን ባለስልጣናት እና ህጋዊ አካላት አስተዋጽዖ ማበርከቱን አስረድተዋል።