የእስራኤል ፕሬዝዳንት የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን ጥልቅ እምነት እና ርህራሄ አስታውሰዋል!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “የጥልቅ እምነት እና ወሰን የለሽ ርኅራኄ የነበራቸው፣ ድሆችን ለማንሣት እና በችግር በተሞላ ዓለም ሰላምን ለማስፈን ሕይወታቸውን የሰጡ ሰው ነበሩ። በትክክል፣ ከአይሁድ ዓለም ጋር የነበራቸውን ግንኙነት በማጠናከር እና በሃይማኖቶች መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ የላቀ መግባባት እና መከባበር መንገድ እንዲደርስ በማስተዋወቅ ላይ ትልቅ ቦታ ሰጥተዋል። በቅድስት ሀገር ያሉ ክርስቲያኖችን አበረታተዋል" ሲሉ ተንግረዋል።
የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣን በመቀጠል “በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም እንዲሰፍን እና በተለይም አሁንም በጋዛ ታግተው ላሉ እስረኞች እንዲመለሱ ያቀረቡት ጸሎት በቅርቡ አዎንታዊ ምላሽ እንደሚያገኝ ከልቤ ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል።
ፕሬዘደንት ሄርዞግ በመቀጠል “ታላቅ መንፈሳዊ አባት ብፁዕ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በማጣታቸው ልባዊ ሀዘናቸውን" ገልጸዋል።
በእየሩሳሌም የሚገኘው ሐዋርያዊ ልዑክ እና የእስራኤል አገር ሊቀ ጳጳስ አዶልፎ ቲቶ ኢላና ለኦስሰርቫቶሬ ሮማኖ ጋዜጣ እንዲህ ብለዋል፡- “ከኦፊሴላዊው መልእክት የበለጠ፣ በተለይ ፕሬዝደንት ሄርዞግ የሚወክሉትን አገር በመወከል ባደረጉት የሐዘን መግለጫ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ዲፕሎማሲው የሐዘን መግለጫ በጥልቅ ነክቶኛል። ለኢየሩሳሌም እውቅና ሰጥተዋል" ብለዋል።